Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ታናሽና ታላቅ በዚያ አሉ፥ አገልጋይም ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ትንሹም ትልቁም በዚያ ይገኛል፤ ባሪያው ከጌታው ነጻ ወጥቷል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ታናናሽና ታላላቅ ሰዎች በአንድነት ይገኛሉ፤ ባሪያዎችም በዚያ ከጌቶቻቸው ነጻ ይወጣሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ታና​ሹና ታላቁ በዚያ አሉ፤ ጌታ​ውን ያገ​ለ​ገለ ባሪ​ያም በዚያ አለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ታናሽና ታላቅ በዚያ አሉ፥ ባሪያም ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።

See the chapter Copy




ኢዮብ 3:19
13 Cross References  

ለሞት፥ ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና።”


ለሰዎችም አንድ ጊዜ ለመሞት ከዚያም ለፍርድ መቅረብ ተመድቦባቸዋል።


አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።


ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥


መንፈስን ለማገድ በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ላይ ሥልጣን የለውም፥ በጦርነትም ውስጥ መሰናበቻ የለም፥ ክፋትም ሠሪውን አያድነውም።


አሕዛብ ሁላችሁ፥ ይህን ስሙ፥ በዓለም የምትኖሩትም ሁላችሁ፥ አድምጡ፥


በዚያ ግዞተኞች በአንድነት ተዘልለው ተቀምጠዋል፥ የአስጨናቂውን ድምፅ አይሰሙም።


በመከራ ላሉት ብርሃን፥ ነፍሳቸው መራራ ለሆነችባቸው፥


የሸለቆው ጓል ይጣፍጥለታል፥ በኋላውም ሰው ሁሉ ይከተለዋል፥ በፊቱም ቍጥር የሌለው ጉባኤ አለ።


በአፈር ውስጥ በአንድ ላይ ይተኛሉ፥ ትልም ይከድናቸዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements