Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 28:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ለጨለማ ወሰን ይደረጋል፥ የጨለማውንና የሞት ጥላን ድንጋይ እስከ ጫፍ ድረስ ይፈላልጋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሰው፣ እስከ ጨለማ መጨረሻ ይዘልቃል፤ ከድቅድቅ ጨለማ የማዕድን ድንጋይ ለማግኘት፣ እስከ ውስጠኛው ዋሻ ገብቶ ይፈልጋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሰዎች ጨለማን በማስወገድ እስከ መሬቱ ጥልቀት ዘልቀው በመግባት ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ውስጥ በመግባት በድቅድቅ ጨለማው ውስጥ የማዕድን ድንጋይ ይፈልጋሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ለጨ​ለማ ወሰ​ንን ያደ​ር​ጋል፤ እርሱ ሁሉን ይመ​ረ​ም​ራል፥ የጨ​ለ​ማ​ንና የሞት ጥላ ድን​ጋ​ይ​ንም ይመ​ረ​ም​ራል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሰው ለጨለማ ፍጻሜን ያደርጋል፥ የጨለማውንና የሞት ጥላን ድንጋይ እስከ ወሰኑ ድረስ ይፈላልጋል።

See the chapter Copy




ኢዮብ 28:3
11 Cross References  

ከሰማይም በታች የተደረገውን ሁሉ በጥበብ እፈልግና እመረምር ዘንድ ልቤን አተጋሁ፥ ይደክሙባት ዘንድ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጣት ከባድ ጥረት ናት።


ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ ስለ ብልኃቱ አመሰገነው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፥ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።


እነሆ፥ አሕዛብ ለእሳት እንደሚሠሩ፥ ሕዝቦችም ለከንቱነት እንደሚደክሙ ከሠራዊት ጌታ ዘንድ የሆነ አይደለምን?


እርሷንም እንደ ብር ብትፈልጋት፥ እንደ ተደበቀ ዕንቁም ብትሻት፥


ከጨለማ ውስጥ ጥልቅን ነገር ይገልጣል፥ የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ይለውጣል።”


ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፥ ከቀለጠ ድንጋይም መዳብ ይወጣል።


ሰው ከሚኖርበት ርቀው መውረጃ ይቈፍራሉ በመንገድኞችም ተረስተዋል፥ ከሰዎችም ርቀው እየተንጠለጠሉ ይወዛወዛሉ።


ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፥ ዳመናም ይረፍበት፥ የቀን ጨለማ ያሸብረው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements