Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 24:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የአመንዝራ ሰው ዐይን ጨለማን ይጠብቃል፦ የማንም ዐይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አመንዝራ በዐይኑ ድንግዝግዝታን ይጠባበቃል፤ ‘ማንም አያየኝም’ ብሎ ያስባል፤ ፊቱንም ይሸፍናል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አመንዝራ ሰው የቀኑን መምሸት ይጠባበቃል፤ ማንም ሰው እንዳያየው ፊቱን ይሸፍናል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የአ​መ​ን​ዝ​ራም ዐይን ድግ​ዝ​ግ​ዝ​ታን ይጠ​ብ​ቃል፦ የማ​ንም ዐይን አያ​የ​ኝም ይላል፥ ፊቱ​ንም ይሸ​ፍ​ናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል፦ የማንም ዓይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል።

See the chapter Copy




ኢዮብ 24:15
15 Cross References  

በልቡም እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፥ ፈጽሞም እንዳያይ ፊቱን ሰወረ”።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”


ጌታ አያይም፥ የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም አሉ።


እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለን? ይላሉ።


ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ትሮጥ ነበር እድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።


አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል፤ እኔ ግን ይህንኑ ነገር በቀን ብርሃን በእስራኤል ሁሉ ፊት እገልጠዋለሁ።”


“አታመንዝር።


“ልቤ ወደ ሌላይቱ ሴት ጐምጅቶ እንደሆነ፥ በባልንጀራዬም ደጅ አድብቼ እንደሆነ፥


ከአላዋቂዎች መካከል አስተዋልሁ፥ ከወጣቶችም መካከል አንዱ አእምሮ ጐድሎት አየሁ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements