Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 23:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “ዛሬም ደግሞ የኀዘን እንጉርጉሮዬ ገና መራራ ነው፥ በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ዛሬም ሐዘኔ መራራ ነው፤ እያቃሰትሁ እንኳ እጁ በላዬ ከብዳለች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “አሁንም ልቤ በመረረ ሐዘንና ሮሮ የተሞላ ነው፤ በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “ዛሬም ዘለ​ፋዬ ከእጄ እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ። እጁ​ንም በእኔ ላይ አከ​በደ፥ አስ​ለ​ቀ​ሰ​ኝም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዛሬም ደግሞ የኅዘን እንጕርጕሮዬ ገና መራራ ነው፥ እጁ በልቅሶ ጩኸቴ ላይ ከብዳለች።

See the chapter Copy




ኢዮብ 23:2
12 Cross References  

“ሕይወቴ ሰለቸኝ፥ የኀዘን እንጉርጉሮዬን እለቅቀዋለሁ፥ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።


በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፥ ጉልበቴ በበጋ ትኩሳት ዛለ።


የጥበቡን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ማስተዋሉ እጥፍ ነውና። እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ።”


“ስለዚህም ከመናገር አፌን አልከለክልም፥ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፥ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጐራጉራለሁ።


ኢዮብም መለሰ፤ እንዲህም አለ፦


እርሱን እንዴት እንደማገኘው ምነው ባወቅሁ! ወደ ተቀመጠበትስ ስፍራ ምነው በደረስሁ!


በኃጢአቱም ላይ ዓመፅን ጨምሮአልና፥ በእኛም መካከል በፌዝ ያጨበጭባልና፥ እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ቃላትን ያበዛልና።”


የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ የዐይንህን ምኞት በቅፅበት እወስድብሃለሁ፤ ቢሆንም ግን ዋይታ አታሰማ፥ አታልቅስ፥ እንባህንም አታፍስስ።


ዮድ። እርሱ አሸክሞታልና ዝም ብሎ ለብቻው ይቀመጥ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements