ኢዮብ 21:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እናንተ፦ “እግዚአብሔር በደላቸውን ለልጆቻቸው ይጠብቃል” ብላችኋል። ይልቁንም እራሳቸው ይረዱት ዘንድ ፍዳን ይክፈላቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እናንተ፣ ‘እግዚአብሔር የሰውን ቅጣት ለልጆቹ ያከማቻል’ ትላላችሁ፤ ነገር ግን ያውቀው ዘንድ ለሰውየው ለራሱ ይክፈለው፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “እናንተ ‘እግዚአብሔር በአባቶች በደል ልጆችን ይቀጣል’ ትላላችሁ፤ እስቲ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ራሳቸውን ይቅጣቸው፤ ይህ ከሆነ በደለኛነታቸውን ሊገነዘቡት ይችላሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ልጆቹ ሀብቱን አያገኙም። እግዚአብሔር ብድራቱን ይከፍለዋል። እርሱም ያንጊዜ ያውቃል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እናንተ፦ እግዚአብሔር በደላቸውን ለልጆቻቸው ይጠብቃል ብላችኋል። እነርሱ ያውቁ ዘንድ ፍዳን ለራሳቸው ይክፈል። See the chapter |