Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 20:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፥ ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፥ ፍርሃትም ይወድቅበታል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ቀስቱን ከጀርባው፣ የሚያብለጨልጨውንም ጫፍ ከጕበቱ ይመዝዛል፤ ፍርሀትም ይይዘዋል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ፍላጻውም ዘልቆ በስተጀርባው ይወጣል፤ የሚያብለጨልጨው ጫፉ ጒበቱን በጣጥሶ ያልፋል፤ በታላቅ ፍርሀትም ልቡ ይሸበራል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ቀስ​ቱም በሥ​ጋው ውስጥ ያል​ፋል። ክፉም ነገር በሰ​ው​ነቱ ይመ​ላ​ለ​ሳል፤ ፍር​ሀ​ትም ይወ​ድ​ቅ​በ​ታል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፥ ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፥ ፍርሃትም ይወድቅበታል።

See the chapter Copy




ኢዮብ 20:25
13 Cross References  

ድንጋጤ በዙሪያው ታስፈራዋለች፥ በስተ ኋላውም ሆና ታባርራቸዋለች።


ቀስተኞቹ ከበቡኝ፥ ኩላሊቴንም ቈራረጠ፥ እርሱም አልራራም፥ ሐሞቴን በምድር ላይ አፈሰሰ።


የሚያንጸባርቅ ሰይፌን ከሳልኩ፥ እጄም ለፍርድ ካነሳችው፥ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እመልሳለሁ።


የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ነው፥ በሰላምም ሳለ ቀማኛ ይመጣበታል።


እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን፥ ሰዎችን ለማስረዳት እንጥራለን፤ ስለ ራሳችን ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጥን ነን፤ ለእናንተም ሕሊና የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።


አቤቱ፥ ነፍሴን ለምን ትጥላለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?


እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ በድንጋጤ ጠፉ።


እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፥ ሁልጊዜ ትክክለኛ ፈራጅ ነው፥


ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ታገኘዋለች፥ በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ትነጥቀዋለች።


ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ሽብሮች በኔ ላይ ተሰልፈዋል።


ኢዮአብም፥ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋር ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እባሉጥ ዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።


ከሚታመንበት ድንኳን ይነቀላል፥ ወደ ድንጋጤም ንጉሥ ያስቸኩሉታል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements