Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 18:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ቁጣ ወርሶሃል፥ ስለ አንተ ሲባል፥ ምድር ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ዓለት ከስፋራው ይነቀላልን?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አንተ በቍጣ የነደድህ እንደ ሆነ፣ ምድር ባዶዋን ትቀራለች? ወይስ ዐለት ከስፍራው ይወገዳል?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አንተ ብትቈጣ ራስህን ትጐዳለህ እንጂ በአንተ ቊጣ ምድር ባዶ አትሆንም። አለቶችም ከስፍራቸው አይነቃነቁም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 መከ​ራው ይገ​ባ​ሃል፤ አን​ተስ የሞ​ትህ እንደ ሆነ ምን​ድን ነው? ከሰ​ማይ በታች ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችን? ወይስ ተራ​ራ​ዎች ከመ​ሠ​ረ​ታ​ቸው ይና​ወ​ጣ​ሉን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ቍጣ ወርሶሃል፥ አንተስ የሞትህ እንደ ሆነ፥ ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ዓለት ከስፋራው ይነቀላልን?

See the chapter Copy




ኢዮብ 18:4
13 Cross References  

በቁጣው ቆራረጠኝ፥ እርሱም ጠላኝ፥ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፥ ጠላቴ ዓይኑን አፈጠጠብኝ፥


“ተራራ ሲወድቅ ይጠፋል፥ ዓለቱም ከስፍራው ይፈልሳል፥


ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጄ አኖራለሁ።


እነሆም፥ ርኩስ መንፈስ ይይዘዋል፤ ድንገትም ይጮኻል፤ አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፤ አድቅቆ በጭንቅ ይለቀዋል፤


በተነሣበት ጊዜ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋ ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፏጫል፤ ሰውነቱም ይደርቃል፤ ርኩስ መንፈሱን እንዲያስወጡት ደቀ መዛሙርትህን ጠየቅኋቸው፤ እነርሱ ግን አልቻሉም።”


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


እግዚአብሔርም ዮናስን “ስለዚች የጉሎ ተክል ልትቆጣ ይገባህልን?” አለው። እርሱም፦ “እስከ ሞት ድረስ ልቆጣ ይገባኛል” አለ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።


ተራሮች ይፈልሳሉ፥ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፥ ይላል የሚራራልሽ ጌታ።


በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ላይ ትፈርዳለህን?


አላዋቂውን ሰው ቁጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።


ስለ ምንስ እንደ እንስሶች ተቈጠርን? ስለ ምንስ በዓይንህ ፊት ቀለልን?


“የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥ የእሳቱም ነበልባል ብልጭ አይልም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements