Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 16:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 መጨማተሬ ይመሰክርብኛል፥ ክሳቴም ተነሥቶብኛል፥ በፊቴም ይመሰክርብኛል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የሰውነቴ መጨማደድ ማስረጃ ሆኖብኛል፤ ክሳቴም በእኔ ላይ ተነሥቶ ኃጢአተኛ ነህ ብሎ ይመሰክርብኛል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አሁን ግን የዕ​ብድ ቍር​ጥ​ራ​ጭና ብጥ​ስ​ጣሽ አደ​ረ​ግ​ኸኝ፤ እኔ​ንም መያ​ዝህ ምስ​ክር ሆነ​ች​ብኝ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 መጨማተሬ ይመሰክርብኛል፥ ክሳቴም ተነሥቶብኛል፥ በፊቴም ይመሰክርብኛል።

See the chapter Copy




ኢዮብ 16:8
10 Cross References  

ምስክሮችህን ታድስብኛለህ፥ ቁጣህንም ታበዛብኛለህ፥ ጭፍራ በጭፍራ ላይ ትጨምርብኛለህ።”


አጥንቴ ከቁርበቴና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቀ፥ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።


በሙላት ወጣሁ፥ ጌታም ባዶዬን መለሰኝ፤ ጌታ በእኔ ላይ ሰቆቃን ሲያደርስ፥ ሁሉን የሚችል አምላክ አስጨንቆኛልና፥ ናዖሚ ብላችሁ ለምን ትጠሩኛላችሁ?” አለቻቸው።


እንዲሁም ጉድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም አንዳች እንከን ሳይገኝባት ቅድስትና ነውር የሌለባት አድርጎ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያንን ለራሱ ሊያቀርባ እንደፈለገ፥


ለጻድቁ ክብር ይሁን የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እኔ ግን፦ ከሳሁ፥ ከሳሁ፥ ወዮልኝ! ከሀዲዎች ክህደትን ፈጽመዋል፤ ከሀዲዎች አስከፊ ክህደት ፈጽመዋል አልሁ።


ስለዚህ ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤ ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ይለኰሳል።


ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ፥ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።


የለመኑትንም ሰጣቸው፥ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።


ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ መላ ሰውነቴ እንደ ጥላ ሆነ።


ሥጋው እስከማይታይ ድረስ ይሰለስላል፥ ተሸፍኖ የነበረውም አጥንት ይገለጣል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements