Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 15:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እጁን በእግዚአብሔር ላይ ዘርግቶአልና፥ ሁሉን የሚችል አምላክን ደፍሮአልና፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እጁን በእግዚአብሔር ላይ አንሥቷልና፤ ሁሉን ቻዩን አምላክም ደፍሯል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “ይህም የሚሆነው እጁን በእግዚአብሔር ላይ አነሣ፤ ሁሉን የሚችለውንም አምላክ ተዳፈረ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እጁን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዘር​ግ​ቶ​አ​ልና፥ ሁሉን በሚ​ችል አም​ላክ ፊትም አን​ገ​ቱን አደ​ን​ድ​ኖ​አ​ልና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እጁን በእግዚአብሔር ላይ ዘርግቶአልና፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ ላይ ደፍሮአልና፥

See the chapter Copy




ኢዮብ 15:25
28 Cross References  

በእኔ ላይ የድፍረት ቃላትን ተናግራችኋል፥ ይላል ጌታ። እናንተ ግን፦ በአንተ ላይ የተናገርነው ምንድነው? ትላላችሁ።


በሰማይ ላይ በድፍረት ተናገሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፥ ከድንኳንም ይነቅልሃል ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።


ተግባራቸውንና መተላለፋቸውን በትዕቢትም እንደሚሠሩም ይናገራቸዋል።


ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ እርሱንስ ተዳፍሮ በደኅና የቆየ ማን ነው?


ግብፃውያንና ፈርዖን እንዳደረጉት ልባችሁን የምታደነድኑት ለምንድን ነው? እነርሱ እስራኤላውያንን የለቀቋቸው እርሱ በጽኑ ከቀጣቸው በኋላ አይደለምን?


ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያንጊዜ የጌታ መልአክ መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።


በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው።


“ጌታ ሆይ! ማን ነህ?” አለው። እርሱም “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይብስብሃል፤” አለው።


እሾህና ኩርንችት ቢያበቅልብኝ፥ እኔ አልቈጣም፥ በእነርሱ ላይ ተራምጄ አቃጥላቸዋለሁ።


እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለን? ይላሉ።


“በእነዚህም ተቀጥታችሁ ወደ እኔ ባትመለሱ፥ ይልቁንም እኔን በመቃወም ብትሄዱ፥


እንዳትለቅቃቸው አሁንም በሕዝቤ ላይ ትታበያለህ፤


መከራና ጭንቀት ያስፈራሩታል፥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥ ያሸንፉታል።


በደንዳና አንገቱና በወፍራሙ ጋሻው እየገሠገሠ ወደ እርሱ ይመጣበታልና፥


ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?


ስለ ይሁዳም ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ በል፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ አንተ፦ “የባቢሎን ንጉሥ በእርግጥ ይመጣል ይህችንም አገር ያፈርሳታል፥ ከሰውና ከእንስሳም ባዶ ያደርጋታል በማለት ለምን ጻፍህበት?” ብለህ ይህን ክርታስ አቃጥለሃል።


ቁጣህን በእግዚአብሔር ላይ እስከ ማንሣት ደርሰህ፥ እነኚህንም ቃላት ከአፍህ እስከ ማውጣት ደርሰህ።


በጌታ ላይ ኰርቶአልና አስክሩት፤ ሞዓብም በጥፋቱ ላይ ይንከባለላል፥ ደግሞም መሳቂያ ይሆናል።


ባቢሎን ሆይ! አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ ከጌታ ጋር ስለ ታገልሽ ተገኝተሻል ተይዘሻልም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements