Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 14:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥ እንዲሁም የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ውሃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ ጐርፍም ዐፈርን ዐጥቦ እንደሚወስድ፣ አንተም የሰውን ተስፋ ታጠፋለህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ውሃ ድንጋይን እየቦረቦረ እንደሚጨርስ፥ ኀይለኛ ዝናብም መሬትን እንደሚሸረሽር፥ አንተም እንዲሁ የደካማን ሰው ተስፋ ታጠፋለህ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “ውኆች ድን​ጋ​ዮ​ችን ይፍ​ቃሉ፤ ፈሳ​ሾ​ቹም የም​ድ​ሩን አፈር ይወ​ስ​ዳሉ፤ እን​ዲሁ አንተ የሰ​ውን ተስፋ ታጠ​ፋ​ዋ​ለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥ እንዲሁ የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።

See the chapter Copy




ኢዮብ 14:19
11 Cross References  

እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እነሆ፦ “አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመን ተቆርጠናል” ይላሉ።


እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በወሰደ ጊዜ፥ አምላክን የካደ ሰው ተስፋው ምንድነው?


በዚህና በዚያም አፈረሰኝ፥ እኔም ሄድሁ፥ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቀለው፥


ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ይቸኩላሉ፥ ያለ ተስፋም ያልቃሉ።”


እነሆ፥ እኔ ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት፥ በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፥ በምድር ያለ ሁሉ ይጠፋል።


“ተራራ ሲወድቅ ይጠፋል፥ ዓለቱም ከስፍራው ይፈልሳል፥


ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፥ መሠረታቸውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።”


እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ነው? ተስፋዬንስ የሚያይ ማን ነው?


Follow us:

Advertisements


Advertisements