Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 14:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፥ ሰውም ነፍሱ ትወጣለች፥ እርሱስ ወዴት አለ?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሰው ግን ይሞታል፤ ክንዱንም ይንተራሳል፤ ነፍሱም ትወጣለች፤ ከእንግዲህስ የት ይገኛል?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሰው ግን ሞቶ እንዳልነበረ ይሆናል፤ ከሞተ በኋላስ የት ይገኛል?

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሰው ግን ከሞተ ፈጽሞ ይተ​ላል፤ ሟች ሰው ከሞተ በኋላ እን​ግ​ዲህ አይ​ኖ​ርም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፥ ሰውም ነፍሱን ይሰጣል፥ እርሱስ ወዴት አለ?

See the chapter Copy




ኢዮብ 14:10
20 Cross References  

ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንደማይ አውቃለሁ።


ሰውም እንዲሁ ተኝቶ አይነሣም፥ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥ ከእንቅልፉም አይነሣም።


ያዕቆብም ትእዛዙን ለልጆቹ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ እግሮቹን በአልጋ ላይ ሰብስቦ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።


ያን ጊዜም በእግሩ አጠገብ ወደቀች፤ ሞተችም፤ ጐበዞችም ሲገቡ ሞታ አገኙአት፤ አውጥተውም በባሏ አጠገብ ቀበሩአት።


ኢየሱስ እንደገና በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን ሰጠ።


ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል፥ ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል።


የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፥ የሚሸሹበትንም ያጣሉ፥ ተስፋቸውም ነፍስን አሳልፎ መስጠት ነው።”


“ስለምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዐይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ።


በማኅፀን ሳለሁ ስለምን አልሞትሁም? ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ስለምን ፈጥኜ አልጠፋሁም?


አባቶቻችንም ሁሉ እንደ ነበሩ እኛ በፊትህ እንግዶችና መጻተኞች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፥ አይጸናም።


አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፥ አንቀላፍቼ ባረፍሁ ነበር፤


ቢመረምራችሁስ መልካም ይሆንልችኋልን? ወይስ በሰውን እንደምታታልሉ ልታታልሉት ትፈልጋላችሁን?


በውኃ ሽታ ያቈጠቁጣል፥ እንደ አትክልት ቅርንጫፍ ያወጣል።


ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”


እንደ ፋንድያ ለዘለዓለም ይጠፋል፥ ያዩትም፦ ወዴት ነው ያለው? ይላሉ።


ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፥ ሁሉም ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል።


የሰው ልጆች መንፈስ ወደ ላይ እንደሚወጣ የእንስሳም ነፍስ ወደ ታች ወደ ምድር እንደምትወርድ የሚያውቅ ማን ነው?


Follow us:

Advertisements


Advertisements