Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 11:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ሁሉን የሚችል አምላክን ፍጻሜ ልትመረምር ትችላለህን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን? ወይስ ሁሉን ቻዩን አምላክ መርምረህ ትደርስበታለህን?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምሥጢር ማወቅ ትችላለህን? ሁሉን ቻይ አምላክንስ መርምረህ ልትደርስበት ትችላለህን?

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍለጋ ልት​መ​ረ​ምር ትች​ላ​ለ​ህን? ወይስ ሁሉን የሚ​ችል አም​ላክ ወደ ፈጠ​ረው ፍጥ​ረት ፍጻሜ ትደ​ር​ሳ​ለ​ህን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክን ፈጽመህ ልትመረምር ትችላለህን?

See the chapter Copy




ኢዮብ 11:7
23 Cross References  

የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው! መንገዱም የማይታወቅ ነው።


ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለማዊነትን በልቡ ሰጠው።


ጌታ ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፥ ታላቅነቱም የማይመረመር ነው።


ከቅዱሳን ሁሉ ያነስኩ ብሆንም፥ ወሰን የሌለውን የክርስቶስን ባለጠግነት ለአሕዛብ እንድሰብክ፥ ይህ ጸጋ ለኔ ተሰጠ፤


አላወቅህም? አልሰማህም? ጌታ የዘለዓለም አምላክ ነው፤ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፤ አይታክትም፤ ማስተዋሉም አይመረመርም።


የነጐድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነበረ፥ መብረቆች ለዓለም አበሩ፥ ምድር ተናወጠች ተንቀጠቀጠችም።


ሁሉን የሚችል አምላክን እናገኝ ዘንድ አንችልም፥ በኃይል ታላቅ ነው፥ በፍርድና በጽድቅም ሃብታም ነው፤ አይጨቁንምም።


የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን ተአምራት ያደርጋል።


ሊመክረውስ የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልቦና አለን።


ለእኛ ግን እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። መንፈስ፥ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር፥ ሁሉን ይመረምራልና።


ሁሉም ነገር በአባቴ ለእኔ ተሰጥቶአል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅደው በቀር አብን የሚያውቅ የለም።


እነሆ፥ እነኚህ የሥራዎቹ ጫፎች ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ማን ማስተዋል ይችላል?”


“እግዚአብሔር በላይ በሰማያት አይደለምን? ከዋክብትም እንዴት ከፍ ባለ ስፍራ ላይ እንዳሉ ተመልከት።”


እነሆ፥ አንተ በዚህ አቋምህ ትክክል አይደለህም፥ ‘እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣል’ ብዬ እመልስልሃለሁ።


አንተ፦ ‘በፍጹም ለቃሌ መልስ አይሰጥም’ ብለህ፥ ስለምን ከእርሱ ጋር ትከራከራለህ?


እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።


እግዚአብሔር በአስደናቂ ሁኔታ በድምፁ ያንጐደጉዳል፥ እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።


የሆነው ነገር ራቀ፥ እጅግም ጠለቀ፥ መርምሮ የሚያገኘውስ ማን ነው?


እኔ ስለ እግዚአብሔር ሥራዎች አስተምራችኋለሁ፥ ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውን አልሸሽግም።


ዐይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ እይ፥ ከአንተም በላይ ከፍ ያሉትን ደመናት ተመልከት።


ያለ እውቀት ምክርን የሚሰውር ማን ነው? ስለዚህ እኔ የማላስተውለውን፥ የማላውቀውንም ድንቅ ነገር ተናግሬአለሁ።


እውቀትህ እጅጉን ያስደንቃል፥ ከከፍታውም ብዛት ልደርስበት አልችልም።


ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?


Follow us:

Advertisements


Advertisements