Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 11:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የጥበቡን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ማስተዋሉ እጥፍ ነውና። እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ትክክለኛ ጥበብ ባለብዙ ፈርጅ ናትና፣ የጥበብንም ምስጢር ምነው በገለጠልህ! እግዚአብሔር ለኀጢአትህ የሚገባውን እንዳላስከፈለህ ባወቅህ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የጥበብ መንገድ ብዙ ስለ ሆነ፥ ምነው ጌታ የጥበብን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ስለዚህ እግዚአብሔር የቀጣህ፥ ከሚገባህ አሳንሶ መሆኑን ዕወቅ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የጥ​በ​ቡን ኀይል ቢገ​ል​ጥ​ልህ! ባንተ ላይ ያለው እጥፍ ነውና። ያን​ጊ​ዜም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በበ​ደ​ልህ ያገ​ኘህ ትክ​ክል እንደ ሆነ ታው​ቃ​ለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የጥበቡን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ማስተዋሉ ብዙ ነውና። እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ።

See the chapter Copy




ኢዮብ 11:6
21 Cross References  

በክፉ ሥራችንና በታላቁ በደላችን ከደረሰብን ነገር ሁሉ በኋላ፥ አንተ አምላካችን እንደ ኃጢአታችን ብዛት አልቀሠፍኸንም ነገር ግን ትሩፋንን ሰጠኸን።


ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፥ ርኅራኄው አያልቅምና።


ይህ ምስጢር አሁን ለቅዱሳኑ ሐዋሪያትና ለነቢያት በመንፈስ እንደተገለጠው ባለፉት ትውልዶች ለነበሩ አልተገለጠም ነበር።


ይህም በነቢዩ እንዲህ ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፤ “አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ፤”


የእግዚአብሔርንስ ምሥጢር ሰምተሃልን? ጥበብን የግልህ ለማድረግ ትመኛለህን?


ጌታ ለሚፈሩት ወዳጃቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።


በውኑ የእግዚአብሔር ማጽናናት፥ በየውሃትም የተነገረህ ቃል ጥቂት ነውን?


በደልህ ንግግርህን ይመራዋል፥ የተንኰለኞችንም አንደበት ትመርጣለህ።


ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ እርሱንስ ተዳፍሮ በደኅና የቆየ ማን ነው?


“ምስጢሩ ለአምላካችን ለጌታ ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ እንድንከተል ለዘለዓለም ለእኛና ለልጆቻችን ነው።”


እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።


ሰውንም፦ ‘እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፥ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”


ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት!


“በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ፥ በእርሱ ዘንድ ምክርና ማስተዋል አለ።


ክፋትህስ ብዙ አይደለምን? ለዐመፅህም ወሰን የለውም።


እነሆ፥ አንተ በዚህ አቋምህ ትክክል አይደለህም፥ ‘እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣል’ ብዬ እመልስልሃለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements