ኤርምያስ 9:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀስፋቸውምን? ይላል ጌታ፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ታዲያ ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንደዚህ ዐይነቱንስ ሕዝብ፣ አልበቀልምን?” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ታዲያ በዚህ ሁሉ ነገር እነርሱን ልቀጣቸውና እንደነዚህ ያሉትንስ ሕዝብ ልበቀላቸው አይገባኝምን? እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በውኑ ስለዚህ ነገር በመቅሠፍት አልጐበኝምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፥ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን? See the chapter |