Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 8:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነሆ፥ መርዛቸውን አስማት የማያረክሰው እባቦችንና እፉኝቶችን በእናንተ መካከል እልካለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል፥” ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “እነሆ፤ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦችን፣ የአስማተኛ ብልኀት የማይገታቸው እፉኝቶችን እሰድዳለሁ፤ እነርሱም ይነድፏችኋል፤” ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ተጠንቀቁ! እነሆ የአስማተኛ ድግምት ሊገታቸው የማይችል መርዘኛ እባቦችንና እፉኝቶችን በመካከላችሁ እልካለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እነሆ አስ​ማት የማ​ይ​ከ​ለ​ክ​ላ​ቸ​ውን የሚ​ገ​ድሉ እባ​ቦ​ችን እሰ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይነ​ድ​ፉ​አ​ች​ኋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እነሆ፥ አስማት የማይከለክላቸውን እባቦችንና እፉኝቶችን እሰድድባችኋለሁ፥ እነርሱም ይነድፉአችኋል።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 8:17
9 Cross References  

ደጋሚ ሳይደግምባት እባብ ብትነድፍ ለደጋሚው ትርፍ የለውም።


በሚያቃጥል ንዳድና በራብ ያልቃሉ፤ በወረርሽኝ መቅሠፍት ይጠፋሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችን፥ ከሚሳቡ መርዘኛ እባቦችን ጋር እሰድባቸዋለሁ።


ጌታም በሕዝቡ ላይ እባቦችን ላከ፥ ሕዝቡንም ነደፉ፤ ከእስራኤልም ብዙ ሰዎች ሞቱ።


የፈረሶቹ ሥልጣን በአፋቸውና በጅራታቸው ነውና፥ ጅራታቸው እባብን ይመስላል፤ ራስም አላቸው፤ በእርሱም ጉዳትን ያደርሳሉ።


በቀርሜሎስም ራስ ላይ ቢሸሸጉ እንኳ አድኜ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ እንኳ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፤


ከአንበሳ ፊት ሲሸሽ ድብ እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው።


ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።


አስማተኛ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements