Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 7:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድርም አራዊት መብል ይሆናል፥ የሚያስፈራራቸውም የለም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ የሚያባርራቸውም አይኖርም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ሬሳቸውም የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ አስፈራርቶ የሚያባርርላቸውም አይኖርም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 የዚህ ሕዝብ ሬሳ ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል፥ የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው የለ​ምና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል፥ የሚያስፈራራቸውም የለም።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 7:33
19 Cross References  

ርስቴ እንደ ዝንጉርጉር አሞራ ሆነችብኝን? አሞሮችስ በዙሪያዋና በላይዋ ሆነዋልን? ሂዱ፥ የምድር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፥ እንዲበሉም አምጡአቸው።


ሬሳህ የሰማይ አሞሮችና የምድር አራዊት መብል ይሆናል፤ የሚያባርራቸውም አይኖርም።


አንተ፥ ወታደሮችህና ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ ሁሉ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።


ለጠላቶቻቸው እጅ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።


በዚያም ቀን ጌታ የገደላቸው ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ እንጂ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም።


አህያም እንደሚቀበር ይቀበራል፥ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል።”


በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፥ በጠላቶቻቸውም ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፥ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።


በክፉ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም አይቀበሩምም፥ በመሬትም ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።


ተናገር፥ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰውም ሬሳ እንደ ጉድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።’ ”


በተራራ ላይ ላሉ ነጣቂ ወፎች፥ ለምድርም አውሬዎች ይተዋሉ። ነጣቂ ወፎችም በጋውን ሁሉ ይበጁባቸዋል፤ የምድርም አውሬዎች ክረምቱን ሁሉ ሲበሉት ይከርማሉ።


ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይጣላሉ፤እነርሱንና ሚስቶቻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም፤ ክፋታቸውንም በእነርሱ ላይ አወርድባቸዋለሁ።


ሰይፍን ለመግደል፥ ውሾችንም ለመጐተት፥ የሰማያትንም ወፎች የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ ዐራቱን ዓይነት ጥፋት ልኬባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።


አንተንና የወንዞችህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥላለሁ፤ በሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ አትከማችም፥ አትሰበሰብም፤ ምግብ እንድትሆን ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች እሰጥሃለሁ።


የጌታ የአምላካችሁን ቃል ስላልሰማችሁ፥ ጌታ ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው እንደ አሕዛብ ሁሉ እንዲሁ እናንተም ትጠፋላችሁ።


ሕፃናቱን ከመንገድ ጉልማሶቹንም ከአደባባይ ለማጥፋት ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ ንጉሥ ቅጥሮቻችን ውስጥ ገብቶአል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements