Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አሕዛብ ሆይ! ስለዚህ ስሙ፤ ማኅበር ሆይ! በእነርሱ ምን እንደሚደርስባቸው እወቁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንግዲህ ሕዝቦች ሆይ ስሙ፤ እናንተም ምስክሮች ምን እንደሚገጥማቸው አስተውሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “እናንተ ሕዝቦች ስሙ! በሕዝቤ ላይ የማደርገውንም ሁሉ አስተውሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አሕ​ዛ​ብና የመ​ን​ጋው ጠባ​ቂ​ዎች ሆይ፥ ስለ​ዚህ ስሙ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አሕዛብ ሆይ፥ ስለዚህ ስሙ፥ ማኅበር ሆይ፥ እነዚያ የሚያገኛቸውን እወቁ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 6:18
9 Cross References  

ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደውን፥ የቤዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፥ የጌታን ጽድቅ እንድታውቅ ከሺጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ የሆነውን እባክህን አስታውስ።


አሕዛብ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውጁ፦ “እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል” በሉ።


እኔም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ፥ አንተ በእውነት ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ፦ ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ አታለልህ” አልሁ።


“እናንት በኢየሩሳሌም የምትኖሩና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፤ በእኔና በወይኔ ቦታ መካከል እስቲ ፍረዱ።


እኔም፦ ‘የመለከቱን ድምፅ አድምጡ’ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ፤ እነርሱ ግን፦ ‘አናደምጥም’ አሉ።


ምድር ሆይ! ስሚ፤ እነሆ፥ ቃሎቼን ስላልሰሙ ሕጌንም ስለ ጣሉት፥ በዚህ ሕዝብ ላይ የሐሳባቸውን ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ።


ለአሕዛብ አሳውቁ፦ “እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውጁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements