ኤርምያስ 52:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን የሕዝቡን ድኆች፥ በከተማይቱም ውስጥ የተረፈውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የተረፉትንም የእጅ ሞያተኞች አፈለሰ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዘረዳን አንዳንድ የድኻ ድኾችንና በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብና ሸሽተው ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን ሰዎች ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ጋራ አፈለሳቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዛርዳን ከሕዝቡ መካከል በጣም ድኻ የሆኑትን፥ በከተማ ውስጥ ቀርተው የነበሩትን፥ በመክዳት ወደ ባቢሎን ሠራዊት ተጠግተው የነበሩትንና ከእጅ ባለሙያዎች መካከል ቀርተው የነበሩትን ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የአዛዦቹም አለቃ ናቡዛርዳን የሕዝቡን ድኆች፥ በከተማም ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የሕዝቡንም ቅሬታ አመጣ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን የሕዝቡን ድኆች፥ በከተማም ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የሕዝቡንም ቅሬታ አፈለሰ። See the chapter |