ኤርምያስ 51:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)49 ለባቢሎን በምድሪቱ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ወድቀዋል እንዲሁ ለእስራኤል ተወግተው ለሞቱት ባቢሎን መውደቅ አለባት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም49 “በምድር ሁሉ የታረዱት፣ በባቢሎን ምክንያት እንደ ወደቁ፣ ባቢሎንም በእስራኤል በታረዱት ምክንያት መውደቅ ይገባታል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም49 ባቢሎን ለዓለም ሕዝብ እልቂት ምክንያት ሆናለች፤ ለብዙ እስራኤላውያን እልቂት ምክንያት በመሆንዋም እነሆ ባቢሎን ራስዋ መውደቅ አለባት፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)49 ባቢሎንም በእስራኤል ስለ ተገደሉት ትወድቃለች፤ ስለ ባቢሎንም በምድር ሁሉ የተገደሉት ይወድቃሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)49 ባቢሎንም ከእስራኤል ተወግተው የሞቱት እንዲወድቁ እንዳደረገች፥ እንዲሁ በባቢሎን ከምድሩ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ይወድቃሉ። See the chapter |