ኤርምያስ 51:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሙግትሽን እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፤ ባሕርዋንም አደርቀዋለሁ ምንጭዋንም እንዲደርቅ አደርጋለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም36 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እሟገትልሻለሁ፣ በቀልሽንም እኔ እበቀልልሻለሁ፤ ባሕሯን አደርቃለሁ፣ የምንጮቿንም ውሃ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ስለዚህ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “እኔ እናንተን እረዳለሁ፤ ባቢሎናውያንንም እበቀልላችኋለሁ፤ የባቢሎን የውሃ ምንጭና ወንዞችዋ ሁሉ እንዲደርቁ አደርጋለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ የሚገፋሽን እፈርድበታለሁ፤ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፤ ባሕርዋንም ድርቅ አደርገዋለሁ፤ ምንጭዋንም አደርቃለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፥ ባሕርዋንም ድርቅ አደርገዋለሁ ምንጭዋንም አደርቀዋለሁ። See the chapter |