Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 51:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 የወንዙም መሻገርያዎች ተይዘዋል፥ የውኃ ማቆርያዎቹም በእሳት ተቃጥለዋል ወታደሮቹም በሽብር ውስጥ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 መልካዎቿ እንደ ተያዙ፣ የወንዝ ዳር ምሽጎቿ እንደ ተቃጠሉ፣ ወታደሮቿም እንደ ተደናገጡ ሊነግሩት ይሯሯጣሉ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 የጠላት ሠራዊት የወንዙን መሸጋገሪያ ይዞ የዘብ መጠበቂያዎቹን አቃጠለ፤ የባቢሎን ወታደሮች በመሸበር ተርበደበዱ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 መሻ​ገ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተይ​ዘ​ዋ​ልና፥ ቅጥ​ር​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አ​ልና፥ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ተማ​ር​ከ​ዋ​ልና።”

See the chapter Copy




ኤርምያስ 51:32
7 Cross References  

የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኃይላቸውም ደክሙአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መቀርቀሪያዎችዋም ተሰብረዋል።


ቀላዩም፦ “ደረቅ ሁን፥ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ” እላለሁ፤


እነሆ፥ እንደ እብቅ ይሆናሉ፥ እሳትም ያቃጥላቸዋል ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኃይል አያድኑም፤ እርሱም ሰው እንደሚሞቀው ፍም፥ ወይም በፊቱ ሰው እንደሚቀመጥበት እሳት ዓይነት አይደለም።


ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንደኛው ሯጭ ሌላውን ሯጭ አንዱም መልእክተኛ ሌላውን መልእክተኛ ለመገናኘት ይሮጣል።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ ዐውድማ ነች፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።”


የከተማይቱም ቅጥር ተጣሰ፥ ወታደሮችም ሁሉ ሸሹ፥ በሁለቱም ቅጥሮች መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማይቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ዓረባም በሚወስደው መንገድ ሄዱ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements