Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 51:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ከአንተም ለማዕዘንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይ አይወስዱም፥ ለዘለዓለምም ባድማ ትሆናለህ፥ ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከአንቺ ለማእዘን የሚሆን ድንጋይ፣ ለመሠረትም የሚሆን ዐለት አይወሰድም፤ ለዘላለም ባድማ ትሆኛለሽ፤” ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ለማእዘን ወይም ለመሠረት የሚያገለግል ድንጋይ አይገኝብሽም፥ አንቺ ለዘለዓለሙ ምድረ በዳ ትሆኚአለሽ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ከአ​ን​ተም ለማ​ዕ​ዘን የሚ​ሆን ድን​ጋ​ይ​ንና ለመ​ሠ​ረት የሚ​ሆን ድን​ጋ​ይን አይ​ወ​ስ​ዱም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አጠ​ፋ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ከአንተም ለማዕዘንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይ አይወስዱም፥ ለዘላለምም ባድማ ትሆናለህ፥ ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 51:26
10 Cross References  

ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥባቸው የሰውም ልጅ የማያልፍባቸው ምድር ሆኑ።


ባቢሎንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮ ማደሪያ ሰውም የማይቀመጥባት መሣቀቅያና ማፍዋጫ ትሆናለች።


ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ለማድረግ የጌታ አሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጠች ተወራጨችም።


የጃርት መኖርያ የውሃም መቋሚያ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ አደርጋታለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements