Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 50:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ስለዚህ በባቢሎን የምድረ በዳ አራዊት ከተኩላዎች ጋር ይቀመጡባታል፥ ሰጐኖችም ይቀመጡባታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘለዓለም አይቀመጥባትም፥ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 “ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊትና የጅብ መኖሪያ፣ የጕጕትም ማደሪያ ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አይኖርባትም፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም የሚቀመጥባት አይገኝም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 “ስለዚህ የዱር አራዊት ከቀበሮችና ከሰጎኖች ጋር በባቢሎን ይኖራሉ፤ እንዲሁም እስከ መቼም ድረስ ከትውልድ እስከ ትውልድ የሰው መኖሪያ አትሆንም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ስለ​ዚህ የዱር አራ​ዊት ከተ​ኵ​ላ​ዎች ጋር ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ሰጎ​ኖ​ችም ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም፤ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚ​ኖ​ር​ባት የለም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊት ከተኩላዎች ጋር ይቀመጡባታል፥ ሰጐኖችም ይቀመጡባታል፥ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘላለም አይቀመጥባትም፥ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 50:39
12 Cross References  

በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኩሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኩሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤


ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ አደርጋታለሁ።


ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥባቸው የሰውም ልጅ የማያልፍባቸው ምድር ሆኑ።


ከአንተም ለማዕዘንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይ አይወስዱም፥ ለዘለዓለምም ባድማ ትሆናለህ፥ ይላል ጌታ።


የጃርት መኖርያ የውሃም መቋሚያ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ሕዝብ ከሰሜን በእርሷ ላይ ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፥ የሚቀመጥባትም አይገኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements