Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 50:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 እርሷ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፥ እነርሱም በጣዖታቱ ላይ እንደ እብድ ይሆናሉና ድርቅ በውኆችዋ ላይ ይሆናል እነርሱም ይደርቃሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ድርቅ በውሆቿ ላይ መጣ! እነሆ፤ ይደርቃሉ፤ ምድሪቱ በፍርሀት በሚሸበሩ አማልክት፣ በጣዖትም ብዛት ተሞልታለችና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ባቢሎን በአጸያፊና ሰውን በሚያሳብድ ጣዖት የተሞላች ስለ ሆነች ወንዞችዋ ሁሉ ይድረቁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 እር​ስዋ የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች ምድር ናትና፥ እነ​ር​ሱም በደ​ሴ​ቶ​ችዋ ይመ​ካ​ሉና ሰይፍ በው​ኆ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ር​ቃሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 እርስዋ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናት፥ እነርሱም በጣዖታት ይመካሉና ድርቅ በውኆችዋ ላይ ይሆናል እነርሱም ይደርቃሉ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 50:38
19 Cross References  

ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።


በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውጁም፥ ዓላማውንም አንሡ፤ አውጁ፥ ሳትደብቁም እንዲህ በሉ፦ ባቢሎን ተያዘች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ተሰባበረ፤ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ተሰባበሩ።


ቀላዩም፦ “ደረቅ ሁን፥ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ” እላለሁ፤


ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን ምስሎችዋን የምቀጣበት በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጋው የሚያቃስትበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ምድርዋም ሁሉ ያፈረች ትሆናለች ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።


በግምባርዋም “ታላቂቱ ባቢሎን፥ የአመንዝሮችና የምድር ርኩሰት እናት” የሚል ምስጢራዊ የሆነ ስም ተጻፈ።


ጳውሎስም በአቴና ሲጠብቃቸው ሳለ፥ በከተማው ጣዖት መሙላቱን እየተመለከተ መንፈሱ ተበሳጨበት።


በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይነጉዱም፥ የባቢሎንም ቅጥር ወድቆአል።


ባቢሎን በጌታ እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፥ አሕዛብም ከወይን ጠጅዋ ጠጥተዋል፤ ስለዚህ አሕዛብ እንደ እብድ ሆነዋል።


እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፥ የወለደቻችሁም ትዋረዳለች፤ እነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ኋለኛይቱ ትሆናለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር በረሀም ትሆናለች።


የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፥ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፥ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ፥ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፤


እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥


የከተማይቱም ሰዎች ኢዮአስን፥ “የበኣልን መሠዊያ ያፈረሰና በአጠገቡ የቆመውን የአሼራን ምስል ዐምድ የሰበረው ልጅህ በመሆኑ መሞት ስላለበት አውጣልን አሉት።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements