ኤርምያስ 50:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የጌታ በቀል ነውና በዙሪያዋ ሆናችሁ በእርሷ ላይ ጩኹ፤ እጅዋን ሰጠች፤ ግንቦችዋ ወደቁ ቅጥሮችዋም ፈረሱ፤ እርሷን ተበቀሉ እንደ ሠራችውም ሥሩባት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ከየአቅጣጫው ጩኹባት፤ እጇን ትሰጣለች፤ ምሽጓም ይወድቃል፤ ቅጥሮቿ ይፈርሳሉ። ይህ የእግዚአብሔር በቀል ነውና፣ እርሷን ተበቀሏት፤ በሌሎቹ ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 በከተማይቱ ዙሪያ በማቅራራት ደንፉ! እነሆ ባቢሎን እጅዋን ሰጥታለች፤ ግንቦችዋ ተጥሰዋል፤ ቅጽሮችዋም ፈራርሰዋል፤ ባቢሎናውያንን እበቀላለሁ፤ እናንተም ተበቀሉአቸው፤ በሌሎች ላይ የፈጸሙትን ጭካኔ በእነርሱም ላይ ፈጽሙባቸው፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 እጆችዋ ደክመዋልና ክበቡአት፤ ግንቧ ወድቋል፤ ቅጥርዋም ፈርሶአል፤ የእግዚአብሔርም በቀል ነውና ተበቀሏት፤ እንደ ሠራችውም ሥሩባት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የእግዚአብሔር በቀል ነውና በዙሪያዋ ጩኹባት፥ እጅዋን ሰጠች፥ ግንቦችዋ ወደቁ ቅጥሮችዋም ፈረሱ፥ እርስዋን ተበቀሉ እንደ ሠራችውም ሥሩባት። See the chapter |