ኤርምያስ 5:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፤ እንደ ወፍ አጥማጆችም ያደባሉ፥ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 “በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና፤ ወፍ እንደሚያጠምዱ ሰዎች፣ ወጥመድ ዘርግተው ሰው እንደሚይዙ ሰዎችም ያደባሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 “በሕዝቤ መካከል የሚኖሩ ክፉ ሰዎች አሉ፤ እነርሱም ወፎችን በወጥመድ እንደሚይዝ ሰው ናቸው፤ ስለዚህ ሰዎችን ለማጥመድ መረባቸውን ዘርግተው ያደባሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፤ ሰዎችንም ይዘው ይገድሉ ዘንድ ወጥመድን ይዘረጋሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፥ እንደ አጥማጆችም ያደባሉ፥ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ። See the chapter |