ኤርምያስ 49:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፥ ወደ እነዚያም ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች ተሰድደው ያልደረሱበት ሕዝብ አይገኝም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም36 ከአራቱ የሰማይ ማእዘናት፣ በኤላም ላይ አራቱን ነፋሳት አመጣለሁ፤ ወደ አራቱም ነፋሳት እበትናቸዋለሁ፤ ከኤላም የሚማረኩት የማይደርሱበት፣ አገር አይገኝም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ከየአቅጣጫውም የሚመታት ነፋስ በዔላም ላይ አስነሣለሁ፤ ሕዝቧንም በየስፍራው እበትናለሁ፤ በዚህም ዐይነት የእርስዋ ስደተኞች የማይኖሩበት አገር አይገኝም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፤ ወደ እነዚያም ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች የማይደርሱበት ሕዝብ አይገኝም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፥ ወደ እነዚያም ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፥ ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች የማይደርሱበት ሕዝብ አይገኝም። See the chapter |