Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 48:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ሞዓብ ሆይ! ወዮልህ! የካሞሽ ሰዎች ጠፍቶአል፤ ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፥ ሴቶች ልጆችህም ወደ ምርኮ ሄደዋልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ተደምስሷል፤ ወንዶች ልጆችህ በምርኮ ተወስደዋል፤ ሴቶች ልጆችህም ተግዘዋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ለሞአብ ሕዝብ ወዮላችሁ! ካሞሽ ለተባለው ጣዖት የሚሰግዱ ሕዝብ ተደመሰሱ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም ተማርከው ተወሰዱ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ሞአብ ሆይ! ወዮ​ልሽ! የካ​ሞሸ ወገን ጠፍ​ቶ​አል፤ ወን​ዶች ልጆ​ችሽ ተማ​ር​ከው ተወ​ስ​ደ​ዋ​ልና፥ ሴቶች ልጆ​ች​ሽም ወደ ምርኮ ሄደ​ዋ​ልና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የካሞሽ ወገን ጠፍቶአል፥ ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፥ ሴቶች ልጆችህም ወደ ምርኮ ሄደዋልና።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 48:46
7 Cross References  

ሞዓብ ሆይ! ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ሆይ! ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፥ ሴቶች ልጆቹንም ለምርኮ፥ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ።


የእስራኤልም ቤት መተማመኛቸው በነበረችው በቤቴል እንዳፈረ፥ እንዲሁ ሞዓብ በካሞሽ ያፍራል።


በሥራሽና በመዝገብሽ ታምነሻልና አንቺ ደግሞ ትያዢያለሽ፤ ካሞሽም ከካህናቱና ከአለቆቹ ጋር በአንድነት ተማርኮ ይሄዳል።


ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ አጸያፊዎች ለሆኑት ኬሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን አዘጋጀላቸው።


አምላክህ ካሞሽ የሰጠህን ይዞ ማቈየቱ ያንተ ፈንታ አይደለምን? እኛስ እንደዚሁ አምላካችን ጌታ የሰጠንን ሁሉ ርስት አድርገን ልንወርስ አይገባንምን?


እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኲሰት ተራራ በስተ ደቡብ ዐስታሮት ተብላ ለምትጠራው ለሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞዓብ አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞን አምላክ ንጉሥ ሰሎሞን አሠርቶአቸው የነበሩት አጸያፊዎች ምስሎች ሁሉ የረከሱ መሆናቸውን አስገነዘበ።


ከጎጆቸው ተበትነው እንደሚበሩ ወፎች፥ የሞዓብ ሴቶችም በአርኖን መሻገሪያዎች እንዲሁ ይሆናሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements