Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 48:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ! ከተሞችን ትታችሁ በዓለት ንቃቃት መካከል ተቀመጡ፥ በገደል አፋፍም ቤትዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ ሁኑ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፤ ከከተማ ወጥታችሁ በዐለት መካከል ኑሩ፤ በገደል አፋፍ ላይ ጐጆዋን እንደምትሠራ፣ እንደ ርግብ ሁኑ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 “የሞአብ ነዋሪዎች ሆይ! ከተሞቻችሁን ለቃችሁ በገደል አፋፍ ጎጆዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ በመሆን በቋጥኞች መካከል ኑሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 በሞ​አብ የሚ​ኖሩ ከተ​ሞ​ችን ትተው በዓ​ለት ውስጥ ተቀ​መጡ፤ በገ​ደል አፋ​ፍም ቤቷን እን​ደ​ም​ት​ሠራ እንደ ርግብ ሆኑ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፥ ከተሞችን ትታችሁ በዓለት ውስጥ ተቀመጡ፥ በገደል አፋፍም ቤትዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ ሁኑ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 48:28
10 Cross References  

በዓለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ፥ ድምፅሽ መልካም ፊትሽም ያማረ ነውና መልክሽን አሳዪኝ፥ ድምፅሽንም አሰሚኝ።


እስራኤላውያን የምድያማውያን ኃይል ስለበረታባቸው በየዋሻውና በየምሽጉ፥ በየተራራው ጥግ መሸሸጊያ ስፍራ አበጁ።


በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ማሣቀቅያህና የልብህ ኩራት አታልለውሃል። ምንም እንኳ ጎጆህን እንደ ንስር ጎጆ ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።


በርራ እንድትወጣ ለሞዓብ ክንፍ ስጡአት፤ ከተሞችዋም ሰው የማይኖርባቸው ባድማ ይሆናሉ።


ጌታ ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፤ ሰዎች ከአስፈሪነቱ ከግርማውም የተነሣ፤ ወደ ዐለት ዋሻ ወደ መሬትም ጉድጓድ ለመሸሸግ ይሮጣሉ።


እስራኤላውያን ያሉበት ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና ሠራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፥ በየዋሻውና በየቁጥቋጦው፥ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጉድጓዱ ሁሉ ተሸሸጉ።


ደግሞም ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት፤ ዳግመኛም ወደ እርሱ ሳትመለስለት ቀረች።


የዔሳውን ጥፋት እርሱን በምጐበኝበት ጊዜ አመጣበታለሁና፥ እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ! ሽሹ፥ ወደ ኋላ ተመለሱ፥ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements