ኤርምያስ 48:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ከእንግዲህ ወዲህ የሞዓብ ትምክሕት የለም፤ በሐሴቦን ሆነው፦ ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት፥ ብለው ክፉ ነገር አስበውባታል። መድሜን ሆይ! አንቺ ደግሞ በጸጥታ ትዋጫለሽ ሰይፍም ያሳድድሻል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ከእንግዲህ ሞዓብ አትከበርም፤ ሰዎች በሐሴቦን ተቀምጠው፣ ‘ኑ ያቺን አገር እናጥፋት’ ብለው ይዶልቱባታል። መድሜን ሆይ፤ አንቺም ደግሞ ጸጥ ትደረጊያለሽ፤ ሰይፍም ያሳድድሻል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 የሞአብ ክብር ያልፋል፤ ሰዎች ሐሴቦንን ለመጣል ያሤራሉ፤ ‘ኑ ከእንግዲህ በሕዝብነት እንዳትታወቅ እናጥፋት’ ይላሉ፤ እናንተም የማድሜን ሰዎች ሆይ! ሰይፍ ስለሚያሳድዳችሁ ጸጥ እንድትሉ ትደረጋላችሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ከእንግዲህ ወዲህ የሞአብ ፈውስ የለም፤ በሐሴቦን ላይ፥ “ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት” ብለው ክፉ ነገርን አስበውባታል። ፈጽሞ ትተዋለች፤ ከኋላዋ ሰይፍ ይመጣልና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ከእንግዲህ ወዲህ የሞዓብ ትምክሕት የለም፥ በሐሴቦን ላይ፦ ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት ብለው ክፉ ነገር አስበውባታል። መድሜን ሆይ፥ አንቺ ደግሞ ትጠፊአለሽ ሰይፍም ያሳድድሻል። See the chapter |