Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 46:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ነፍሳቸውንም በሚሽዋት ሰዎች እጅ፥ በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፥ በባርያዎቹም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ አንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች፥ ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ነፍሳቸውን ለሚሹት ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆርና ለጦር መኰንኖቹ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ግብጽ እንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች” ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሊገድሉአቸው ለሚፈልጉ ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ለሠራዊቱ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሆኖም ዘግየት ብሎ ከዚህ በፊት እንደሆነው ሁሉ ግብጽ እንደገና የሰዎች መኖሪያ ትሆናለች፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ፈ​ልጉ ሰዎች እጅ፥ በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ እንደ ቀድ​ሞው ዘመን የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ነፍሳቸውንም በሚፈልጉ ሰዎች እጅ፥ በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፥ በባሪያዎቹም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፥ ከዚያም በኋላ አንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች፥ ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 46:26
7 Cross References  

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው ነፍሱንም ለሚሻው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፥ እንዲሁ፥ እነሆ፥ የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ለጠላቶቹ ነፍሱንም ለሚሽዋት እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።”


ነገር ግን በኋለኛው ዘመን የኤላምን ምርኮ እመልሳለሁ፥ ይላል ጌታ።”


ነገር ግን በኋለኛው ዘመን የሞዓብን ምርኮ እመልሳለሁ፥ ይላል ጌታ።” የሞዓብ ፍርድ እስከዚህ ድረስ ነው።


ግብጻውያንንም ለጨካኝ ገዢዎች አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል፥ ይላል ልዑል የሠራዊት ጌታ።


“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፥ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements