Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 46:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የግብጽ ሴት ልጅ ታፍራለች፤ ለሰሜኑ ሕዝብ ተላልፋ በእጃቸው ትሰጣለች።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የግብጽ ሴት ልጅ ለኀፍረት ትጋለጣለች፤ ለሰሜን ሕዝብም ዐልፋ ትሰጣለች።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የግብጽ ሕዝብ በሰሜን ሕዝብ ስለሚሸነፉ ያፍራሉ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የግ​ብፅ ልጅ ታፍ​ራ​ለች፤ በሰ​ሜን ሕዝብ እጅም አልፋ ትሰ​ጣ​ለች።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የግብጽ ልጅ ታፍራለች፥ በሰሜን ሕዝብ እጅ አልፋ ትሰጣለች።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 46:24
6 Cross References  

እነሆ፥ እኔ በሰሜን ያሉትን የመንግሥታትን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ፥ ይላል ጌታ፤ እነርሱም ይመጣሉ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌም በር መግቢያ በዙሪያዋም ባለ ቅጥርዋ ሁሉ ላይ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ ዙፋናቸውን ያስቀምጣሉ።


ድንግሊቱ የግብጽ ልጅ ሆይ! ወደ ገለዓድ ውጪ የሚቀባንም መድኃኒት ውሰጂ፤ ብዙ መድኃኒቶችን የተጠቀምሺው በከንቱ ነው፤ ለአንቺ መዳኛ የለሽም።


አንቺ ፈራሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ውኃ ከሰሜን ይነሣል የሚያጥለቀልቅም ጐርፍ ይሆናል፤ በአገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements