ኤርምያስ 46:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 “ጠላቶችዋ በኃይል ዘምተው እንደ እንጨት ቈራጮች በምሳር ይመጡባታልና በደረቱ እንደሚሽሎኮሎክ እባብ ድምፅ ታሰማለች። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ጠላት ገፍቶ ሲመጣባት፣ ግብጽ እንደሚሸሽ እባብ ታፏጫለች፤ ዛፍ እንደሚቈርጡ ሰዎች፣ መጥረቢያ ይዘው ይመጡባታል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22-23 የጠላት ሠራዊት ኀይል ሲቃረብ ግብጽ እንደ እባብ የፉጨት ድምፅ እያሰማች ትሸሻለች፤ ሰዎች ጥቅጥቅ ያለውን ደን እንደሚመነጥሩ በመጥረቢያ አደጋ ይጥሉባታል። የሰዎቻቸው ብዛት በቊጥር አይደረስበትም፤ የወታደሮቻቸውም ብዛት ከአንበጣ ሠራዊት ይበልጣል፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ሠራዊትም በኀይል ይዘምቱባታልና፥ እንደ እንጨት ቈራጮችም በምሳር ይመጡባታልና ድምፅዋ እንደምትሸሽ እባብ ይተማል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ከሠራዊትም ጋር ይሄዳሉና ድምፅ እንደ እባብ ይተምማል፥ እንደ እንጨት ቈራጮችም በምሳር ይመጡባታል። See the chapter |