ኤርምያስ 46:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 እርሱም ብዙዎችን አሰነካከለ፥ እርሱም ደግሞ ወደቀ፤ እርስ በርሳቸውም፦ ተነሡ፥ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባትም ምድር እንመለስ ተባባሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ደጋግመው ይሰናከላሉ፣ አንዱም በሌላው ላይ ይወድቃል፤ ‘ተነሡ እንሂድ፤ ወደ ሕዝባችንና ወደ ትውልድ አገራችን እንመለስ፤ ከጠላትም ሰይፍ እናምልጥ’ ይላሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ጀሌዎቻቸው ተሰናክለው አንዱ በአንዱ ላይ ይወድቃሉ፤ እርስ በርሱም አንዱ ሌላውን፥ ‘ከጠላት ሰይፍ አምልጠን ከሀገራችን ሕዝብ መቀላቀል እንድንችል እንፍጠን’ ይለዋል።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ብዛታቸውም ደከመ፤ ወደቀም፤ አንዱም አንዱ ለጓደኛው፦ ተነሥ፤ ከአረማውያን ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባት ምድር እንመለስ አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ብዛታቸውም ተሰናከለ፥ ሰውም አንዱ በአንዱ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም፦ ተነሡ፥ ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባት ምድር እንመለስ አሉ። See the chapter |