ኤርምያስ 46:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ያ ቀን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ እርሱም ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን ነው፤ ሰይፍ በልቶ ይጠግባል በደማቸውም ይሰክራል፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ያ ቀን ግን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን። ሰይፍ እስኪጠግብ ድረስ ይበላል፤ ጥማቱም እስኪረካ ድረስ ደም ይጠጣል። በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷልና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ይህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የመረጠው ቀን ነው፤ እርሱ ዛሬ የበቀል እርምጃ ይወስዳል፤ ጠላቶቹንም ይቀጣል። የእርሱም ሰይፍ ብዙዎችን ይበላል፤ በደማቸውም ይለወሳል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኙ ምርኮኞቹን መሥዋዕት ያደርጋቸዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ያ ቀን ጠላቶቹን የሚበቀልበት የአምላካችን የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ በልቶ ይጠግባል፤ በደማቸውም ይሰክራል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መሥዋዕት በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ነውና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ያ ቀን ጠላቶቹን የሚበቀልበት የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፥ ሰይፍ በልቶ ይጠግባል በደማቸውም ይሰክራል፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና። See the chapter |