Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 45:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አንተ፦ ‘ጌታ በሕመሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ! በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፥ ዕረፍትንም አላገኘሁም’ ብለሃል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አንተ፣ ‘እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ፤ ከልቅሶዬ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም’ ብለሃል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ሐዘን ጨምሮብኝ ምንም ዕረፍት ሳይኖረኝ በመቃተት ደክሜአለሁና ወዮልኝ!

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አንተ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ማሜ ላይ ኀዘ​ንን ጨም​ሮ​ብ​ኛ​ልና ወዮ​ልኝ! በል​ቅ​ሶዬ ጩኸት ደክ​ሜ​አ​ለሁ፤ ዕረ​ፍ​ት​ንም አላ​ገ​ኘ​ሁም ብለ​ሃል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አንተ፦ እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ! በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፥ ዕረፍትንም አላገኘሁም ብለሃል።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 45:3
28 Cross References  

መልካምን ሥራ ለመሥራት አንታክት፥ ካልዛልን ወቅቱ በደረሰ ጊዜ እናጭዳለንና።


ስለዚህ አንታክትም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየመነመነ ቢሄድ እንኳን፥ ውስጣዊው ሰውነታችን በየዕለቱ ይታደሳል።


ስለዚህ ይህ አገልግሎት የተሰጠን በእግዚአብሔር ምሕረት ምክንያት ስለሆነ፥ መቼም አንታክትም።


እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ።


ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራልና፥


ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና። ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኃጢአቴ ሁሉ እንዳደረግህብኝ አድርግባቸው።


ሜም። ከላይ እሳትን ወደ አጥንቴ ሰደደ በረታችበትም፥ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም ቀኑንም ሁሉ አደከመኝ።


ተወግተው ስለ ሞቱት ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን እንዳለቅስ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!


ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል።


በመከራ ቀን ብትዝል፥ በእርግጥም ጉልበትህ ትንሽ ነው ማለት ነው።


መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፥ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ።


በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቆሚያም የለኝም። ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ።


አምላኬ ሆይ፥ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች፥ ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስታውስሃለሁ።


የጌታን ቸርነት በሕያዋን ምድር እንደማይ አምናለሁ።


በሞት የሚያስታውስህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?


“ዛሬም ደግሞ የኀዘን እንጉርጉሮዬ ገና መራራ ነው፥ በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት።


“ባሮክ ሆይ! የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይልሃል፦


በመቃተቴ ደክሜአለሁ፥ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን በእንባ አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements