Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 42:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እናንተ የይሁዳ ትሩፍ ሆይ! ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአችኋል፦ ወደ ግብጽ አትግቡ፤ ዛሬ እንዳስጠነቀቅኋችሁ በእርግጥ እወቁ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤ እግዚአብሔር፤ ‘ወደ ግብጽ አትሂዱ’ ብሏችኋል፤ እኔም ዛሬ እንዳስጠነቀቅኋችሁ በርግጥ ዕወቁ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19-20 “እናንተ ከስደት የተረፋችሁ የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር በላካችሁኝ ጊዜ እርሱ የሚያዘውን ሁሉ ንገረንና እንፈጽማለን ብላችሁ የማትፈጽሙትን ቃል በመግባታችሁ አደገኛ ስህተት ሠርታችኋል፤ አሁንም እግዚአብሔር ወደ ግብጽ አትሂዱ ብሎ ስለ ከለከለ እኔም ዛሬ ይህ ትእዛዝ እርግጠኛ መሆኑን በመግለጥ አስጠነቅቃችኋለሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ግብፅ አት​ግቡ ብሎ ተና​ግ​ሮ​ባ​ች​ኋ​ልና ዛሬ እን​ዳ​ስ​ጠ​ነ​ቀ​ቅ​ኋ​ችሁ በእ​ር​ግጥ ዕወቁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፥ እግዚአብሔር፦ ወደ ግብጽ አትግቡ ብሎ ተናግሮባችኋልና ዛሬ እንዳስጠነቀቅኋችሁ በእርግጥ እወቁ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 42:19
17 Cross References  

ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ ፈረሰኞች ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ ጌታ፥ ‘በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ’ ብሎአችኋልና።


“ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቆጡህ።


አስቀድመን ደግሞ እንደ ነገርናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


እንግዲህ አሕዛብ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ፥ በጌታም እለምናችኋለሁ።


በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ፤” ብሎ መከራቸው።


ነገር ግን በእርሱ ላይ ዐመጸ፥ ፈረሶችንና ብዙ ሕዝብም እንዲሰጡት መልእክተኞቹን ወደ ግብጽ ላከ። ይሳካለታልን? እነዚህን ነገሮች ያደረገስ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንን አፍርሶስ ያመልጣልን?


ነገር ግን ጻድቁን ኃጢአት እንዳይሠራ ብታስጠነቅቀው፥ ጻድቁም ኃጢአት ባይሠራ፥ ተጠንቅቆአልና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፥ አንተም ነፍስህን አድነሃል።


እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ በመካከላቸው ነቢይ እንደ ነበረ ያውቃሉ።


ለመውጣት እንቢ ብትል ግን፥ ጌታ ያሳየኝ ነገር ይህ ነው።


ወደ ጌታም እንዲመልሱአቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፥ እነርሱ ግን አላደመጡም።


ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዝሙር ምስክር ይሆንባቸዋል። በዘራቸው የሚረሳ አይደለምና። ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገ ባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳን አስቀድሜ ዐውቃለሁ።”


ጌታም በሰይፍ እንድንሞት ወደዚች ምድር ለምን ያገባናል? ሚስቶቻችንና ልጆቻችን ለምርኮ ይሆናሉ፤ ወደ ግብጽ መመለስ አይሻለንምን?”


ጉበኛውም፦ “ይነጋል ደግሞም ይመሻል፤ ትጠይቁ ዘንድ ብትወድዱ ጠይቁ፤ ተመልሳችሁም ኑ” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements