ኤርምያስ 40:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 አይሁድ ሁሉ ከተሰደዱበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ፤ ወደ ይሁዳም አገር ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ መጡ፤ ወይንና የበጋንም ፍሬ እጅግ ብዙ አከማቹ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ሁላቸውም ከተበታተኑበት አገር ሁሉ ወደ ይሁዳ ምድር ተመለሱ፤ በምጽጳ ወደሚኖረውም ወደ ጎዶልያስ መጡ፤ ወይንና የበጋ ፍሬም በብዛት አከማቹ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ስለዚህም ተበታትነው የሚኖሩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ትተው ወደ ይሁዳ ተመለሱ፤ በምጽጳ ወደሚገኘው ወደ ገዳልያም መጥተው እጅግ ብዙ የሆነ የወይን ዘለላና የሌላውንም ተክል ፍሬ በመሰብሰብ አከማቹ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 አይሁድም ሁሉ ከተሰደዱበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ፤ ወደ ይሁዳም ሀገር ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ መሴፋ መጡ፤ ወይንንና የበጋን ፍሬ፥ ዘይትንም እጅግ ብዙ አከማቹ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 አይሁድ ሁሉ ከተሰደዱበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ፥ ወደ ይሁዳም አገር ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ መጡ፥ ወይንና የበጋንም ፍሬ እጅግ ብዙ አከማቹ። See the chapter |