Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 37:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ‘የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች አገር ላይ አይመጣም’ ብለው ትንቢት ለእናንተ ይናገሩ የነበሩ ነብዮቻችሁ ወዴት አሉ?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ለመሆኑ፣ ‘የባቢሎን ንጉሥ እናንተንም ይህችንም ምድር አይወጋም’ ብለው ትንቢት ይናገሩ የነበሩት ነቢያታችሁ ወዴት ናቸው?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ለመሆኑ ‘የባቢሎን ንጉሥ በአንተም ሆነ በአገርህ ላይ አደጋ አይጥልም’ ብለው የነገሩህ ነቢያትህ አሁን የት አሉ?

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በእ​ና​ን​ተና በዚ​ህች ሀገር አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም ብለው ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ የነ​በሩ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችሁ ወዴት አሉ?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች አገር አይመጣባችሁም ብለው ትንቢት ይናገሩላችሁ የነበሩ ነቢያቶቻችሁ ወዴት አሉ?

See the chapter Copy




ኤርምያስ 37:19
16 Cross References  

ለራስህ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር ብዛት እንዲሁ ናቸውና እስቲ ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ።


“ወደ ተማረኩት ሁሉ እንዲህ ብለህ ላክ፦ ‘ስለ ኔሔላማዊው ስለ ሸማያ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችኋልና፥ በሐሰትም እንድትታመኑ አድርጎአችኋልና፥


ለሚንቁኝ ሁልጊዜ፦ ጌታ፦ ሰላም ይሆንላችኋል ብሏል ይላሉ፤ በልቡም እልከኝነት ለሚሄድ ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያገኛችሁም ይላሉ።


የሕዝቤንም ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን፦ ‘ስለም ሰላም’ ይላሉ።


የሕዝቤንም ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን፦ ‘ሰላም ሰላም’ ይላሉ።


ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ ኢዮራምን፥ “እኔ አንተን የምረዳህ ስለምንድን ነው? ሄደህ አባትህና እናትህ ይጠይቁአቸው የነበሩትን እነዚያን ነቢያት ጠይቅ!” አለው። ንጉሥ ኢዮራምም መልሶ፥ “አይደለም እኮ! ሦስታችንንም ነገሥታት ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ለመስጠት የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ።


ኖን። ነቢዮችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፥ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፥ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።


እነዚያ የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥ የመጠጥ መለማመኛቸውንም ወይን የጠጡ? እስቲ እነርሱ ይነሡና ይርዱአችሁ! እስቲ መጠጊያም ይሁኑላችሁ!’”


የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት በሚናገሩ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፥ ከገዛ ልባቸውም ትንቢት የሚናገሩትን እንዲህ በላቸው፦ የጌታን ቃል ስሙ፤


ጌታ ሳይልካቸው፦ ጌታ ይላል የሚሉ ሰዎች ከንቱ ነገርንና ውሸተኛ ሟርትን አይተዋል፥ ሆኖም ቃላቸው እንዲፈጸም ይጠብቃሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements