Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 36:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ስለዚህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከእርሱም በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይኖረውም፥ ሬሳውም በቀን ለፀሐይ ሐሩርና በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፤ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከዘሩ አይገኝም፤ ሬሳውም ወደ ውጭ ተጥሎ ለቀን ሐሩርና ለሌሊት ቍር ይጋለጣል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ንጉሥ ኢዮአቄም ሆይ! እነሆ እግዚአብሔር ስለ አንተ የሚለው ይህ ነው፦ ‘ከዘርህ በዳዊት መንግሥት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከቶ አይኖርም፤ ሬሳህም የትም ተጥሎ ለቀን ፀሐይ ሐሩርና ለሌሊት ቊር የተጋለጠ ይሆናል፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ስለ​ዚ​ህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​አ​ቄም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዳ​ዊት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጥ ልጅ አይ​ኖ​ር​ለ​ትም፥ ሬሳ​ውም በቀን ለት​ኩ​ሳት፥ በሌ​ሊ​ትም ለው​ርጭ ይጣ​ላል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ስለዚህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀማጭ አይኖርለትም፥ ሬሳውም በቀን ለትኩሳት በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 36:30
7 Cross References  

ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”


እንዲህ ስሆን፥ የቀን ሐሩር የሌሊት ቁር ይበላኝ ነበር፥ እንቅልፍም ከዓይኔ ጠፋ።


በወደዱአቸውና ባገለገሉአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፤ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።


ኢዮአቄምም እንዳደረገው ሁሉ በጌታ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር አደረገ።


ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements