Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 36:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ባሮክም፦ “እነዚህን ቃላት ከአፉ ይነግረኝ ነበር፥ እኔም በመጽሐፉ ላይ በቀለም እጽፍ ነበር” ብሎ መለሰላቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ባሮክም፣ “አዎን ይህን ሁሉ በቃሉ ነገረኝ፤ እኔም በብራናው ላይ በቀለም ጻፍሁ” ብሎ መለሰላቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ባሮክም “በእርግጥ ቃሉን አንድ በአንድ የነገረኝ ኤርምያስ ነው፤ እኔም በዚህ ብራና ላይ በቀለም ጻፍኩት” አላቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ባሮ​ክም፥ “ኤር​ም​ያስ ይህን ቃል ከአፉ ይነ​ግ​ረኝ ነበር፤ እኔም በመ​ጽ​ሐፉ ላይ እጽፍ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ባሮክም፦ ይህን ቃል ከአፉ ይነግረኝ ነበር፥ እኔም በመጽሐፉ ላይ በቀለም እጽፍ ነበር ብሎ መለሰላቸው።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 36:18
7 Cross References  

ኤርምያስም የኔርያን ልጅ ባሮክን ጠራ፥ ባሮክም ኤርምያስ እየነገረው ጌታ ለእርሱ የተናገረውን ቃላት ሁሉ በመጽሐፉ ክርታስ ጻፈ።


“አንድ የመጽሐፍ ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን፥ ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ ለአንተ የተናገርሁትን ቃላት ሁሉ ጻፍበት።


ንጉሡም ኤርምያስ ለባሮክ እየነገረው የጻፈውን ቃላት የያዘውን ክርታስ ካቃጠለ በኋላ የጌታ ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦


ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ፥ ለኔርያም ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው፤ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃላት ሁሉ ኤርምያስ እየነገረው ጻፈበት፥ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ተመሳሳይ ብዙ ቃላት ተጨመረበት።


በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የኔርያ ልጅ ባሮክ ኤርምያስ በቃል እየነገረው እነዚህን ቃሎች በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ፥ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements