ኤርምያስ 36:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ባሮክም የኤርምያስን ቃላት በላይኛው አደባባይ በጌታ ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ፥ በገማርያ ጓዳ በጌታ ቤት ውስጥ በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ ከመጽሐፉ አነበበ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ባሮክም በብራና ላይ የተጻፈውን የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ፤ “አዲሱ በር” በሚባለው በቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ በሚገኘው በጸሓፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል ውስጥ ሆኖ ለሕዝቡ ሁሉ አነበበው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ሕዝቡም ለማዳመጥ በሚችልበት ሁኔታ ባሮክ እኔ የነገርኩትን በብራና ጽፎት የነበረውን ቃል ሁሉ አነበበላቸው። በቤተ መቅደስ ውስጥ ይህን ያደረገው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል በኩል ዘልቆ ነበር፤ ክፍሉም የሚገኘው ወደ ቤተ መቅደስ ከሚያስገባው አዲስ የቅጽር በር አጠገብ በላይኛው አደባባይ በኩል አለፍ ብሎ ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ባሮክም የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ በእግዚአብሔር ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሓፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ በመጽሐፉ አንበበ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ባሮክም የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ በእግዚአብሔር ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ጓዳ በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ በመጽሐፉ አነበበ። See the chapter |