ኤርምያስ 34:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ቃል ኪዳኔንም የተላለፉትን ሰዎች፥ እንቦሳውንም ቈርጠው በቁራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳኑን ሕግጋት ያልፈጸሙትን፥ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ኪዳኔን ያፈረሱትንና በፊቴ የገቡትን የኪዳኑን ቃል ያልፈጸሙትን ሰዎች ሥጋውን ሁለት ቦታ ከፍለው በመካከሉ እንዳለፉት፣ እንደ እንቦሳው አደርጋቸዋለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ባሪያዎቻችሁን ነጻ ለማውጣት በፊቴ ቃል ኪዳን በገባችሁ ጊዜ አንድን ጥጃ በመቊረጥ ለሁለት ከፍላችሁ በመካከሉ አልፋችኋል፤ ነገር ግን እናንተ ያን ቃል ኪዳንና እኔም ከእስራኤል ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሳችኋል፤ ስለዚህ እናንተ በጥጃው ላይ እንዳደረጋችሁት እኔ በእናንተ ላይ አደርጋለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ቃል ኪዳኔን የተላለፉትን ሰዎች፥ በፊቴ ያደረጉትን ቃል ኪዳን ያልፈጸሙትን፥ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ያለፉትን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ቃል ኪዳኔንም የተላለፉትን ሰዎች፥ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳንን ቃል ያልፈጸሙትን፥ See the chapter |