ኤርምያስ 34:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰምተው ማንም ሰው ወንድ ባርያውንና ሴት ባርያውን አርነት እንዲያወጣ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ማንም እንዳይገዛቸው አደረጉ፤ እነርሱም ሰምተው አርነት አወጡአቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 በዚህ ቃል ኪዳን የተስማሙት ባለሥልጣኖችና ሕዝቡ ሁሉ ወንድ ወይም ሴት ባሪያዎቻቸውን ነጻ ለመልቀቅና ከእንግዲህ ባሪያ አድርገው ላይገዟቸው ተስማሙ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ሕዝቡና መሪዎቻቸው ሁሉ ባሪያዎቻቸውን ነጻ ለመልቀቅና እንደገና መልሰውም ባሪያዎች ላለማድረግ ተስማሙ፤ በዚህም ስምምነት መሠረት ሁሉንም ነጻ አወጡአቸው፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ሰው ሁሉ ወንድ ባሪያውንና ሴት ባሪያውን አርነት እንዲያወጣ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ማንም እንዳይገዛቸው ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ፤ አርነትም አወጡአቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ሰው ሁሉ ወንድ ባሪያውንና ሴት ባሪያውን አርነት እንዲያወጣ ከእንግዲህ ወዲህም ማንም እንዳይገዛቸው ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ አርነትም አወጡአቸው። See the chapter |