ኤርምያስ 33:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 እንዲሁም ሌዋውያን ካህናት በእኔ ፊት የሚቃጠለውን መሥዋዕት የሚያቀርብ፥ የእህሉንም ቁርባን የሚያቃጥል፥ ሁልጊዜም የሚሠዋ ሰው ፈጽሞ አያጡም።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ሌዋውያን ከሆኑት ካህናትም የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ፣ የእህል ቍርባን ለማቃጠልና ሌላውንም መሥዋዕት ለመሠዋት ሁልጊዜ በፊቴ የሚቆም ሰው አይታጣም።’ ” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 እንዲሁም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የእህል መሥዋዕትና ሌላውንም መሥዋዕት በማቅረብ የሚያገለግሉኝ ካህናት ከሌዊ ወገን ከቶ አይጠፉም።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የሚያቀርብ፥ የእህሉንም ቍርባን የሚያቃጥል፥ ሁልጊዜም የሚሠዋ ሰው ከሌዋውያን ካህናት ዘንድ በእኔ ፊት አይታጣም።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የሚያቀርብ የእህሉንም ቍርባን የሚያቃጥል ሁልጊዜም የሚሠዋ ሰው ከሌዋውያን ካህናት ዘንድ በእኔ ፊት አይታጣም። See the chapter |