Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 32:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እንዳመጣሁ፥ እንዲሁ ለእነርሱ የተናገርሁትን በጎነት ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በዚህ ሕዝብ ላይ ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት እንዳመጣሁ እንደዚሁ ቃል የገባሁላቸውን መልካም ነገር ሁሉ እሰጣቸዋለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 “በሕዝቡ ላይ ይህን ሁሉ ጥፋት እንዳመጣሁባቸው ሁሉ እንዲሁም ቃል የገባሁላቸውን መልካም ነገር እሰጣቸዋለሁ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ዳ​መ​ጣሁ፥ እን​ዲሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ላ​ቸ​ውን በጎ​ነት ሁሉ አመ​ጣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እንዳመጣሁ፥ እንዲሁ የተናገርሁላቸውን በጎነት ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 32:42
8 Cross References  

እንዲህም ይሆናል፤ እነርሱን ልነቅላቸውና ልሰባብራቸው፥ ላፈርሳቸውና ላጠፋቸው፥ ክፉም ላደርግባቸው እንደ ተጋሁ፥ እንዲሁ ልሠራቸውና ልተክላቸው እተጋለሁ፥ ይላል ጌታ።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


የምሠራላቸውንም በጎነት ሁሉ በሚሰሙ የምድር አሕዛብ ሁሉ ፊት ይህች ከተማ ለእኔ የምስጋናና የክብር የደስታም ስም ትሆናለች፤ እኔም ስላደረግሁላት በጎነትና ሰላም ሁሉ ይፈራሉ ይንቀጠቀጣሉም።


“እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።


ከልዑል አፍ ክፉና መልካም ነገር አይወጣምን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements