Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 32:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 “ስለዚህ አሁን ግን የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ አንተ ስለ እርሷ፦ ‘በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ተሰጥታለች’ ስለምትላት ከተማ እንዲህ ይላል፦

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 “ ‘በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር ለባቢሎን ንጉሥ ዐልፋ ትሰጣለች’ ስላልሃት ስለዚህች ከተማ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ኤርምያስ ሆይ! እነሆ ሕዝቡ ‘ይህችን ከተማ ጦርነት፥ ራብና ቸነፈር በባቢሎን ንጉሥ እጅ እንድትወድቅ ሊያደርጉአት ነው’ ይላሉ፤ እነሆ እኔ የምለውን ሌላ ነገር ደግሞ ስማ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ስለ እር​ስዋ፥ “በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትሰ​ጣ​ለች ስለ​ም​ት​ላት ከተማ እን​ዲህ ይላል፦

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 አሁን እንግዲህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አንተ ስለ እርስዋ፦ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ተሰጥታለች ስለምትላት ከተማ እንዲህ ይላል፦

See the chapter Copy




ኤርምያስ 32:36
11 Cross References  

እነሆ፥ አፈር ደልድለው የመሸጉ፥ ከተማይቱን ሊይዙአት ቀርበዋል፤ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም የተነሣ ከተማይቱ ለሚዋጉአት ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች፤ የተናገርኸውም ሆኖአል፥ እነሆም፥ አንተ ታየዋለህ።


የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንዲህ ብሎ አሳስሮት ነበርና፦ “ስለምን እንዲህ ብለህ ትንቢት ትናገራለህ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ እርሱም ይይዛታል፤


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህችን ከተማ ለከለዳውያን እጅና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እርሱም ይይዛታል።


በደል እንዲበዛ ሕግ ገባ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ጸጋ ይበልጥ በዛ፤


እርሷም፦ “ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።


እነሆ፥ በቁጣዬና በመዓቴ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፥ በደኅንነትም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements