ኤርምያስ 32:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ‘አቤቱ ጌታ ሆይ! ወዮ! እነሆ፥ በእውነት አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ለአንተም ከቶ የሚሳንህ ምንም ነገር የለም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “አቤት፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰማያትንና ምድርን በታላቅ ኀይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፤ የሚሳንህም አንዳች ነገር የለም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! በታላቁ ሥልጣንህና ኀይልህ ሰማይና ምድርን ፈጥረሃል፤ ከቶም የሚሳንህ ነገር የለም፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 “ወዮ! አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እነሆ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኀይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፤ ከአንተም የሚሳን ምንም ነገር የለም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም። See the chapter |