ኤርምያስ 31:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ጌታ እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ማረፊያ ሊሻ በሄደ ጊዜ ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ፣ በምድረ በዳ ሞገስን ያገኛል፤ እኔም ለእስራኤል ዕረፍት ለመስጠት እመጣለሁ።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እስራኤል ዕረፍትን ለማግኘት ወደ ፊት በመጣ ጊዜ ከጦርነት የተረፉት በምድረ በዳ የእኔን የእግዚአብሔርን ምሕረት ያገኛሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ። ሂዱ፦ እስራኤልንም አታጥፉ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ማረፊያ ሊሻ በሄደ ጊዜ ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ። See the chapter |