ኤርምያስ 31:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 አሕዛብ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውጁ፦ “እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል” በሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 “ሕዝቦች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ሩቅ ባሉ የባሕር ጠረፎችም፣ ‘እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፤ መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል’ ብላችሁ ዐውጁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሆይ! አድምጡኝ፤ በሩቅ ጠረፎችም ቃሌን ዐውጁ፤ እኔ ሕዝቤን በትኜ ነበር፤ አሁን ግን እሰበስባቸዋለሁ፤ እረኛ መንጋውን እንደሚጠብቅም እጠብቃቸዋለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 አሕዛብ ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና፥ “እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፤ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 አሕዛብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና፦ እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ። See the chapter |